ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ

35ቱ ዋና ዋና አገልግሎቶች ዝርዝር

1. ፕሮጀክቶችን ማዘጋጀትና መገምገም፤
  • የስራ ዕድል መፍጠሪያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ማዘጋጀትና መገምገም
  • ለስራ ዕድል መፍጠሪያ የሚውሉ ፕሮጅቶችን መገምገም
2. የስራ ስምሪት አገልግሎት መስጠት፤
  • በተለዩ የስራ ዕድል አማራጮች የስራ ስምሪት አገልግሎት መስጠት፤
3. ስራ ፈላጊዎችን የመመዝገብ አገልግሎት መስጠት፤
  • ስራ ፈላጊ ዜጎችን ለመመዝገብ የቅስቀሳና ንቅናቄ ስራዎችን ማከናወን
4. የመረጃ ምክርና ግንዛቤ አገልግሎት መስጠት፤
  • የመረጃና የምክር አገልግሎት መስጠት፥
5. ለስራ ፈላጊዎች የቴክኒክና የንግድ ክህሎት ስልጠና አገልግሎት መስጠት፤
  • ስራ ፈላጊዎች የሚፈልጉትን የስልጠና አይነት መለየት
6. ስራ ፈላጊዎችን በኢንተርፕራይዝ የማድራጀት አገልግሎት መስጠት፤
  • ስራ ፈላጊዎችን በኢንተርፕራይዝ የማድራጀት አገልግሎት፣
  • በጥሪት ማፍሪያ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን ድጋፍ በማድረግ ወደ መደበኛ አደረጃጀት ማሸጋጋር፤
7. አገናኝተው ለሚወጡ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና ዕድሳት መስጠት፤
  • አገናኝተው የሚወጡ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት፣
  • አገናኝተው የሚወጡ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ ዕድሳት መስጠት፤
8. አገናኝተው የሚወጡ ኤጀንሲዎችን ቁጥጥር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
  • የክትትልና የቁጥጥር ቼክ ሊስቶችን ማዘጋጀት፣
  • አገናኝተው ከሚወጡ ኤጀንሲዎች ጋር ተያይዞ የሚነሱ አቤቱታዎችና ቅሬታዎችን መፍታት፥
  • ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን መስራት፤
9. ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት በህዝብ ተሳትፎ ለመደገፍ መድረኮችን በክፍለ ከተማ ደረጃ ማዘጋጀት፤
  • የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ የሚሰሩ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ማደራጀት፣
  • በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት አፈጻጸም፣ በተገኙ መልካም ልምዶች ዙሪያ በክፍለ ከተማ ደረጃ የምክክር መድረክ ማካሄድ፣
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን የልየታ ስራ ለመስራት ወረዳዎችን መደገፍ፤
  • የተጠቃሚዎች ማህበራዊ አገልግሎት ትስስር ስራ መስራት
  • በልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚነት የማህበራዊ ተጠያቂነት ማስፈን
10. የቅሬታና አቤቱታ ስርአት መዘርጋት፤
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ የቅሬታ ምንጮችን መለየት የመፍትሄ ሀሳብ ማመንጨትና ስልጠናዎችን መስጠት፤
11. የማህበረሰብ አቀፍ ስራ ተጠቃሚዎች ሊያሰራ የሚያስችል ቦታ በመስለየት ማሰራትና ተጠቃሚ ማድረግ፤
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች መረጃ በዩፓስ ማደራጀት፤
  • በአካባቢ ልማት ስራዎች ጋይድላይን ላይ ስልጠና መስጠት
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ የማህበረሰብ ልማት ስራዎች ሰሪ ሀይሎችን ወደ ስራ ማስገባት፣ በማሰራት፣ ተጠቃሚ ማድረግ እና ድጋፍና ክትትል ማድረግ
12. የኑሮ ማሻሻያ የድጋፍ ማዕቀፎች መስጠት፤
  • የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ጥሪት ማፍሪያ ላይ ማሰማራት፣
  • የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች በተለያዩ የግብርና እና ከግብርና ውጪ ባሉ የገቢ ማስገኛ ስራዎች እንዲሰማሩ እና ጥሪት እንዲጨምሩ ማድረግ
  • የአካባቢ ልማት ስራዎች ከቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻያ ስራዎች እና ከሰርዓተ-ምግብ ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ ለማድረግ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት
  • የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች አዋጭ የስራ ዘርፍ ላይ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
  • የኑሮ ማሻሻያ የድጋፍ ማእቀፎችን እንዲያገኙ ማድረግ፤
13. የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ማቋቋም ና ማጠናከር፤
  • የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ማጠናከር
  • የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት እንዲፈፀም ማድረግ
  • ለአንድ ማዕከላት በፍረጃው መሰረት የማበረታቻ፣ እውቅና እና ሽልማት አሰራርን መዘርጋት፤
  • የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ የህግ ማዕቀፎች (ደንብ፤ መመሪያ፣ የማስፈጽሚያ ማንዋሎችን) መገምገምና ግብዓት መስጠት
  • የአንድ ማዕከላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፤
  • የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍና ለማዘመን በቴክኖሎጅ የተደገፈ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት የሚያስችል ግብዓ መስጠጥ
  • የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ግንባታዎችን ክትትል ማድረግ፤
  • በተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች ለስራ ፈላጊዎችና ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ አገልገሎቶችን በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ውስጥ እንዲሰጡ ማድረግ፤
14. ስልጠና የሚሰጡባቸውን ስርዓተ ስልጠና የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች (ሞጁሎች) ማሰራጨት፤
  • ስልጠና የሚሰጡባቸውን ስርዓተ ስልጠና የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች (ሞጁሎች) ማሰራጨት
15. ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ በልማታዊ ሴፍቲኔት የፕሮጀክት ማበልጸጊያ እና ማስተግበሪያ ሰነድ ዙሪያ ለአመራርና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት
  • ለሚሰሩ የአካባቢ ልማት ስራዎች የሴፍጋርድ/ማህበራዊና አካባቢያዊ ደህንነት/ መጠበቅ ስራ መስራት
  • በፕሮጀክቱ የመሰረተ ልማት ስራዎች ተጠቃሚዎችን ወደ ስራ ማስገባት
  • በክፍለ ከተማ ደረጃ የመሰረተ ልማት ግንባታ ግብዓት ፍላጎት መለየት
  • የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚ ቤተሰቦችን እና የገንዘብ ስጦታ የሚያገኙ ተጠቃሚዎችን መለየት
16. የፕሮግራም ማደስ ፤ማስፋፋት እና ዕውቅና የማግኘት አቅማቸውን ማሳደግ፤
  • ከየቤተሰቡ አንድ ተወካይ እንዲመርጡ ለማድረግ ግንዛቤ በመፍጠር እንዲለዩ ማድረግ
  • በኑሮ ማሻሻያ የድጋፍ ማዕቀፎች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፤
17. በተቋማትና ሰልጣኞች ያሉ አለመግባባቶች በጋራ እንዲፈቱ ማድረግ፤
  • በግል ለመስራት የሚፈልጉትን ተጠቃሚዎች የመለየት ስራ በመስራት የስራ ፍለጋ እቅድ እንዲያቅዱ ማድረግ
  • ቴክኒካል ስልጠና የሚያስፈልጋቸውን የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎችን ስልጠናውን እንዲያገኙ ማድረግ
18. የሱፐርቪዥን እና ቁጥጥር አገልግሎት መስጠት፤
  • ለተጠቃሚዎች በሰለጠኑት የስራ ዘርፍ የብቃት ማረጋገጫ /COC/ እንዲያገኙ አሰራር ስርዓት መዘርጋት
19. ከኢንዱስትሪውና ባለድርሻ ጋር ትስስር በመፍጠር የውጤት ተኮር ስርዓቱን ማጎልበት፤
  • የምክርና እና ድጋፍ አገልግሎት ሞጁል ዙርያ መስጠት፥
  • የኑሮ ማሻሻያ የገንዘብ ስጦታ/Grant/ የሚያገኙ ተጠቃሚዎችን ለመለየት ዝግጅት ማድረግ
  • የኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች የፋይዳ ግምገማ ማድረግ፤
20. ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ስርአት መዘርጋትና ማስተዳደር፤
21. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የህግ ማእቀፎች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥና የሙያ ደህንነትና ጤንነት መጠበቁን ለመከታተል ቁጥጥር ማድረግ፤
  • የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ የህግ ማዕቀፎች ተፈፃሚነት ማረጋገጥ፤
  • የሠራተኞች ደህንነት፣ጤንነትና የስራ አካባቢ እንዲጠበቅ ማድረግ
22. በህግ ማእቀፎች ፖሊሲዎች እና በሙያ ደህንነት ጤንነት አጠባበቅ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት፤
  • የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ
  • በሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ግንዛቤ ማስጨበጥ
  • የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይን የሚመለከቱ የዓለም አቀፍ ክብረ በዓላትን በኢንዱስትሪው ማህበረሰብ ንቅናቄ በመፍጠር ማክበር
23. የሥራ ሁኔታ መረጃ መሰብሰብ፣ማደራጀት፣መተንተንና ስታትስቲካል መጽሄት በማዘጋጀት ማሰራጨት፤
  • ለሴፍቲ ኮሚቴ ምዝገባና እውቅና መስጠት
  • የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት ምዝገባና እውቅና አገልግሎት መስጠት፤
  • የህብረት ስምምነት ምዝገባና ዕውቅና አገልግሎት መስጠት
24. በስራ ቦታ የማህበራዊ ምክክር አሠራሮች ማስተግበር፤
  • የሚቀርቡ የወል የሥራ ክርክሮችንና የህብረት ድርድር ልዩነቶች በስምምነት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ
  • ድጋፍና ክትትል ማድረግ
  • በሥራ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ማካሄድ
  • በማህበራዊ ምክክር አሠራር ጥናት ማካሄድ
25. የማምረት አቅም አጠቃቀም መለካት፤
26. የድርድርና የኮሚሽንኒንግ አገልግሎት መስጠት፤
  • የማሽን ተከላ ሂደትን ማማከር
27. የካፒታል ሊዝ ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት፤
28. የመስሪያ፣ ማሳያ እና መሸጫ ቦታ ማመቻቸት፤
  • ለኢንተርፕራይዞች የመስሪያ፣ ማሳያ እና መሸጫ ቦታ ማመቻቸት፤
  • የመስሪያ ቦታ ተስማሚነት ልየታ ማድረግ ላይ ድጋፍ መስጠት
  • የዘርፍ ማህበራትን ማደራጀት፤
29. የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት፤
  • የንግድ ስራ እቅድ/ቢዝንስ ፕላን መገምገም
30. የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ገበያ ትስስር መፍጠር፤
  • የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር መፍጠር
  • ኢንተርኘራይዞች የውጭ ሀገር ገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት፤
31. ምርትና አገልግሎትን ማስተዋወቅ፤
  • ኤግዚቢሽንና ባዛር ማዘጋጀት
  • የኢንተርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎት በኢምፖሪየም /በምርት ማሳያና መሸጫ ሱቆች/ በማስገባት አንዳስተዋውቁና እንዲሸጡ ማድረግ
  • በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ሱቅ ምርትና አገልግሎት እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ማድረግ
  • ዳይሬክተሪ እና ካታሎግ በማዘጋጀት የኢንርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎት ማስተዋወቅ
32. የግብዓት ትስስር መፍጠር፤
  • የግብዓት እና የምርት ትስስር ማመቻቸት
33. የዕድገት ደረጃ ሽግግር አገልግሎት መስጠት፤
  • የዕድገት ደረጃ ሽግግር መስጠትና መረጃቸውን ማደራጀት
  • የተሰጠዉ የዕድገት ደረጃ ሽግግር ትክክለኛነት በዳሰሳ ጥናት ማረጋገጥ
  • ወደ ከፍተኛ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞችን ማስመረቅ
34. የኦዲት አገልግሎት መስጠት፤
  • የኦዲት አገልግሎት ለመስጠት መረጃ መሰብሰብ
35. ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት፤
  • የሀገር ውስጥ ምርጥ ተሞክሮ መቀመር
  • ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን መለየት
  • ምርጥ ተሞክሮ መለየት
  • የውጪ ሀገር ምርጥ ተሞክሮ መቀመር
  • ምርጥ ተሞክሮ ማስፋት
  • የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣
  • ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ